Abstract:
ኢትዮጵያ ፍትህ እኩልነትና ነፃነት ለሕዝቦቿ ለማጎናፀፍ የሚያስ
ችላትን የሶሻሊዝም ሥርዓት በመገንባት ላይ በመሆኗ " ጤና ለሁሉም "
ለሚለው መፈክር ቅድሚያ ሰጥታለች ፡፡ ይህንንም ሀቅ የምትመራበት የብሔ
ራዊ ዲሞክራሲያዊ አብዮት ፕሮግራም ያረጋግጣል ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ኢት
ዮጵያ " ጤና ለሁሉም እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም. " የሚ
ለውን ዓለም አቀፋዊ መርህ ከተቀበሉ የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት አባል መን
ግሥታት አንዷ ናት ፡፡