Abstract:
ባሳለፍናቸዉ አመታት በሃገር አቀፍ እንዲሁም በጤናዉ ሴክተር የጤና ተቋማትን የጤና አገልግሎት ተደራሽነት
እና ጥራት ለማሻሻል በርካታ የሪፎርም ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡ በመጀመሪያዉ የጤናዉ ዘርፍ
የትራንስፎርሜሽን እቅድ ወቅት በሃገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ በርካታ ግቦችን ለማሳካት
ተችሏል፡፡ ይሁን እንጂ የተገኙ አፈፃፀሞች ላይ ክፍተት የታየባቸዉን ተግባራት እና በዘላቂ ልማት የተቀመጡ
ግቦችን ለማሳካት በሁለተኛዉ ዙር የትራንስፎርሜሽን እቅዳችን አዳዲስ አጀንዳዎች እና በርካታ የማስፈፀሚያ
ስልቶች በጋራ ተነድፈዉ ወደስራ ተገብቷል፡፡ የኢትዮጵ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ፕሮግራምም ከ
2004ዓ/ም ጀምሮ ሲተገበሩ ከቆዩ የማሻሻያ ፕሮግራሞች ዉስጥ የሚጠቀስ ነው፡፡